Tuesday, December 11, 2007

The Lost Boys and his mom story

His name is Simon, 20 years ago when he was about 8 years old a civil war in Sudan irrupted , Simon did not have any choice expect run for his life from his childhood village to Gambela, a small border town to Ethiopia. He was separated from his parents and siblings. He found a refuge shelter in Ethiopian a region called “Gambela”. The only close relative he had at the refugee camp was his uncle, as a lost boy he grew up without a parent and when the Ethiopian government was thrown out by the current government the camp was attacked and they forced to fled to Kenya. While Simon was in Kenya refugee camp one guy told him Simon mom was died. That was another personal loss and devastation for the young Simon, he was crashed, he was depressed and felt lonely more than for ever. His hope to meet his mom was vanished to the air. After several agony years finally he got a chance to immigrate to US and settled in San Diego. SD was his home after Kenya refuge camp.
Because of attractive wages Simon decided to work in Alaska for the fishing company. He said it is a good payment. People can make a year wage in three to four months. Now lonely Simon does not have any one except himself and God. While he was working in the ship one night Simon was sleeping. In the middle of the night a human figure appeared in font of him. It was kind of ghost. It was like the ghost of his mother. Simon was frightened and screamed loud and went crazy. The whole ship crew heard his scream and wake up and rushed to his room. They asked him what happened and told them about his dream. Every one thought this is “ Just a Nightmare” .
But for Simon it was not just a nightmare, but it was real. He could not get rid of it from his mind. Then he decided to call back to Sudan. There was one of his friend in Sudan and he called him and told him to search for his mom. His friend told him he will do what ever he can.
Guess what? His friend told him one of the unbelievable story for Simon. His mom is “ALIVE”
Simon could not waste any time and called to his mom. After 20 years he was able to talk to his mom. Yesterday he came to Yebbo Travel and book his flight to Nairobi and will fly to his village to meet his mom. Unfortunately he found out that his father was alive but died in 2005.
For us the story is priceless. we hope you like the story and make you happy for the day
ስሙ ሳይመን ይባላል፡፡ አሁን ያለው ዜግነት አሜሪካዊ ቢሆንም ትውልዱ ሱዳን ነው፡፡ ሳይምን በአሁኑ ወቅት የጠፉ ልጆች ወይም ሎስት ቦይስ (lost boys) ከሚባሉት በስደት ለብዙ ዘመናት በስደት ላይ ከሚገኙት የደቡብ ሱዳን ዜጎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ሳይመን ለስደት የበቃው የዛሬ 20 አመት የ 8 ልጅ እያለ ነው፡፡ ያኔ በሱዳን በነበረው ጭፍጨፋ ሳይመን ከወላጆቹ እና ከወንድሞቹ ተለይቶ ወደ ጋናቤላ አጎቱን ተከትሎ ይሄዳል፡፡ ጋንቤላ ለብዙ ጊዜ ከተቀመጡ በኋላ ኢትዩጵያ ውስጥ መንግስቱ ለቆ ሲሄድ ወደ ኬንያ ይሰደዳሉ፡፡ አንድ ቀን ከኩኩማ የስደተኞች መንደር እያለ አንዱ ጓደኛው ይመጣና ሳይመንን እናትህ ሞተች ይለዋል፡፡ ሳይመንም እዚያው ድርቅ ብሎ ውሃ ሆኖ ይቀራል፡፡ ከዚያ ነበር ሳይመን ሂዎቱ ዳግም ብቸኛ ባዶ የሆነበት፡፡ ያ ቀን የሳይመን ክፉ ቀን እንደሆነ እስከ አሁን እይኑ እንባ እየቋጠረ ያወራል ከብዙ አመታት የስደት ቆይታ በኃላ ሳይመን ከሌሎች የሱዳን ስደተኞች ጋር ሆኖ ወደ አሜሪካ የመምጣት እድል ያገኛል፡፡ አሜሪካ ሳንድያጎም እንደመጣ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ ከቆዬ በኋላ በአጋጣሚ ጥሩ ስራ ይገኛበታል ከሚባለው አላስካ (Alaska) ከሚሉት ግዛት በመርከብ ላይ ሆኖ አሳ የማጥመድ ስራ አግኝቶ ይሔዳል፡፡ አላስካ ማለት በረዶ ቤት ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው መርከብ ላይ ስራ ከጀመረ መርከቡ ለብዙ ወራት ወደ የብስ ሳይመለስ ራሽያ ለመድረስ ትንሽ ሲቀረው ነው የሚመለሰው፡፡ ብዙ ኢታዮጳያዊያን የስራውን ሁኔታ ሲገልጹ ልብ ወለድ የሚያወሩ ነው የሚመስለው፡፡ መርከቡ 24 ሰዓት ነው የሚሳራው፡፡ ሰራ ካለ መተኛት የለም፣ ሰራ ከሌለ ደግሞ ከዚያው ከመርከቡ ላይ በርን ዘግቶ መተኛት ነው፡፡ ይታያችሁ ቀዝቃዛ፣ ባዶ፣ ጨለማ፣ ከውቅኖስ መሃል፡፡ ከግራ ውሃ፣ ከቀኛ ውሃ፣ ከላይ ውሃ፣ ከታች ውሃ፣ ብርድ አጥንት ቆርጥሞ የሚገባ ብርድ፡፡ ሳይመንም በዚህ የመሬት ፂዎል በሆነ ወና መርከብ ላይ ደክሞት እንደተኛ በጨለማው አናቱ ብቅ ትልበታለች፡፡ ፈረንጆች ጎስት (Ghost) ወይም ዱካክ እንደሚሉት ማለት ነው፡፡ ሳይመንም በድንጋጤ መርከቡን በጩኸት ያደባልቀዋል፡፡ በመርከቡ ያለው ሰራተኛ ሁሉ ከእንቅልፉ ይባንንና ምነው ሲሉት “እናቴን አየኋት” ይላል ታሪኩን ሲነግራቸው ትንሽ ነካ ያደርገዋል ብለው ትተውት ይሄዳሉ፡፡ ሳይመን ግን ያዬው ነገር ከቅዠት የላቀ በመሆኑ ወዲያው ስልክ ሱዳን በቅርቡ ለሄደ ጓደኛው ይደውላል፡፡ ደውሎም እናቱን እንዲፈልግ ይነግረዋል፡፡ ጓደኛም በአጋጣሚ ሱዳን ስለነበር ትንሽ ቆይቶ መልሶ እንዲዳል ለሳይመን ይነግረዋል፡፡ ሳይመንም ሲፈራ ሲችል ሲቸር ከትንሽ ከቆታ በኋላ መልሶ ስልክ ይደውላል፡፡ ታዲያ የአምላክ ነገር ሆኖ ሳይመን ትልቁን ምስራች ደረሰው እናቱ በሂወት መኖሯን ተረዳ፡፡ ወዲያው ከአላስካ እንደተመለሰ ወደ የቦ የጉዞ ወኪል መትቶ በአስቸኳይ ወደ ናይሮቢ ለመጓዝ ጠየቀን፣ እኛም በደስታ ወደ ናሮቢ የሚሄድበትን ትኬት በደቂቃ ውስጥ አዘጋጅተን ሰጠነው፡፡ የአሜሪካው ማስተር ካርድ እንደሚላው ከዚህ አገልግሎት የምናገኘው እርካታ.. ፕራይስለስ ነው፡፡ ትንሽ የሚያሳዝነው አባቱም እስከ 2005 ደረስ በሂዎት እንደቆዩና ሳይገናኑ መቅረታቸውን አና በሞት እንደተለዩ ሲነገረው ወንድሞቹም ደህና መሆናቸውን ለማቅ ችሏል፡፡ የቦ የጉዞ ወኪል ወይም የቦ ቢሮ የሰወችን የጎዞ ማስተናገድ ባቻ ብይሆን ብዙ አገልግሎቶችን የሚሰጥበት ማእከል ነው፡፡ ከዚህ በፊት የተደረጉ ብዙ ደስ የሚሉ አገልግሎቶች ቡኖሩም የዛሬው ግን ትንሽ ለየት ሰለሚል ለንባብ ማብቃቱ ታሪኩን ከእናንተ ጋር ለመካፈል ስለሚያስችለን እስኪ አብረን እናውጋው፡፡

© 2007 Yebbo.com

No comments: