Tuesday, October 24, 2006

ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የጉዞ ወኪሎች ታሪክ በቀን 24 በሳምነት 7 ቀን ክፍት የሆነ የጉዞ ወኪል፡፡
ለመሆኑ የቦ ምንድን ነው?
እንሆ ዛሬ የየቦን ስም ይዘን ትርጉሙን ሳንነግራችሁ ወደ አስር አመት ሊጠጋን ነው፡፡ በነዚሁ አመታት ውስጥ ስለ የቦ ያልደረሰን ጥያቄ የለም፡፡ በሪድዮ፣ በቴሌዥን በጋዜጣ፣ ሰወች በአካል መጥተው፣ በኢሜል እና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሰለየቦ ትርጉም የተጠየቅን ሲሆን፣ የሚገርመው ብዛት ያላቸው ቋንቋች ለየቦ ትርጉም አላቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ የቦ ማለት ጦር፣ ሀይለኛ ውሻ፣ መደሰት እና የመሳሰሉ ለየቦ የተሰጡ ትርጎሞች ናቸው፡፡
ዋናው እና ለእኛ የቦ ለማለት ያስቻለን ስም ግን የመጣው አያት ቅድማያቶቻችን ተወልደው አድገው የተወሰነው ዘር ደግሞ እስከ አሁን ከሚኖርበት ከተቀደሰው እና ከተባረከው የገጠር መንደር የተወሰደ ነው፡፡ የቦ ወይም የቦ ማርያም የሚገኘው በጎጃም ክፍለ ሀገር በደብረማርቆስ አውራጃ ከደብረ ማርቆስ ከተማ በእግር በግምት ወደ ሁለት ሰዓት ከሚወስድ የገጠር ቦታ ላይ ነው፡፡
የቦ ማለት በምድር ላይ ያለ ገነት ማለት ነው፡፡እስከ አሁን ድረስ የሚታየኝ የሰው የዋህነት፣ የእንግዳ አክባሪነት፣ እና ትሁትነት ነው፡፡ የቦ እንደሌላው የኢትዮጵያ ገበሬ ዝናብ ጠብቆ የሚያመርት ሳይሆን በመስኖ እየተጠቀመ አመቱ ሙሉ ለምለም የሆነ ቦታ ነው፡፡ ትርንጎ፣ ሎሚ፣ ቡና፣ ሾላ፣ አሽቃሞ፣ ኮሽም፣ ቃሪያ፣ ቲማቲም፣ በሶ ብላ(ዝቃ ቅቤ)፣ ጠጀ ሳር፣ ፊላ፣ ቄጠማ፣ ባኅር ዛፍ፣ እነጆሪ፣ ዘንባባ፣ እና የመሳሰሉት እፅዋት የተለመዱ ሲሆኑ ገና የውትርንን ወንዝ ተሻግረው ወደ የቦ ሲገቡ የሚቀበልዎ ሽታ ንፁህ፣ በተፈጥሮ ማእዛ ያማረ ጤናማ አየር ነው፡፡
የቦ ማርያም በያመቱ የሚከበር ታላቅ ንግስ (ባዕል) ነው፡፡ የየቦ ማርያም ቀን ሁሌ የሚውለው ፍስለታ ከመግባቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ እሁድ ቀን ነው፡፡ በዚህ ባህል ላይ ለመገኘት ከየቦታ ያሉ ምእመናን ከከተማም ሆነ ከገጠሩ መሄድ የተለመደ ነው፡፡ በዚህ ቀን ማንም ሰው ከማንም ቤት ከብቶ መብላተም ሆነ መጠጣት መብቱ ነው፡፡ የሚገርመው የየቦ ሰው በመንገድ ያለፈውን ሰው ሁሉ እረ ባካች ጠበል ቅመሱ እያለ ቤቱ መጋበዙ ነው፡፡ በመቦቴ አፈር ስሆን እያለ ሰውን ካልበላችሁ ብሎ መለመን የተለመደ ነው፡፡ የቦ አንድን ሰው ሰላም ለማለት ማወቅ አያስፈልገም፡፡ ሰላምታ የእግዚያብሄር ነው ሰለሚባል የተገናኘው ሰው ሁሉ ሰላም ተባባሎ ተሳስቆ ነው የሚለያየው፡፡ ታዲያ የየቦ ማሪያም ቀን ሁሉም ሰው እኩል ነው፡፡ ሁሉም ሰው በፈለገው ቤት ገብቶ ከፈለገው ጓሮ ሄዶ በልቶ ጠጥቶ ሆዱ ሞልቶ ተደስቶ ለዛሬ አመት ያድረሰን ብሎ አመስግኖ ነው የሚሄደው፡፡
ያ ነው የኛ የቦ፡፡የምድር ላይ ገነት፡፡ ሰው የሚዋደድበት፣ ሰው የሚፋቀርበት ሰላም እና ወንድማማችነት የሰፈነበት ቦታ ለመፍጠር፡፡
ታዲያ ያው እንደለመድነው ወደ የቦ ሲመጡ የምንቀበልዎ እንደ እህት እንደ ወንድም፣ እንደ አባት እንደ እናት አድረገን ነው፡፡

በዚህ አጋጣሚ ይህን ወብሳይት ከዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ በሃሳብም ሆነ በማንኛውም ትብብር ላደረጋችሁልን ህዝቦች በጣም እናመሰግናለን፡፡ ባጋጣሚ የቦ ከሄዳችሁ የላካችሁ
የቄሰ ገበዝ ዋሲሁን ልጆች ልይሽ ዋሲሁን፣ የደርሰህ ዋሲሁን፣ የ እውነቱ ዋሲሁን፣ የ ሰዋለም ዋሲሁን፣ የታጫውት ዋሲሁን፣ የአንየው ደርሰህ፣ የበቃሉ ደርሰህ የየውብዳር ደርሰህ፣ ዘር ነው በሉ፡፡
ይህም ወብሳት ከዚህ በላይ ለተጠቀሱት እና ለየቦ ማርያም ህዝቦች ስም የተሰራ ነው፡፡
የቦ፡ የምድር ላይ ገነት

No comments: